top of page
Light Blue and Green Protect Pregnant Women Landscape COVID Flyer.png

COVID-19 ጨርሶ ስላልጠፋ እንዳንዘናጋ

ኮቭድ ጨርሶ ስላልጠፋ እንዳንዘናጋ

ኮቭድ ጨርሶ ስላልጠፋ መዘናጋትን አስወግደን እራሳችንን እና ማህበረሰባችንን መከላከሉን አጠናክረን መቀጠል ይጠበቅብናል

አብዛኛዎቻችሁ በሚገባ እንደምታውቁት የኮሎራዶ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የኮቭድ -19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ከ2019 አንስቶ ከድርጅቶችና ከመንግስት ተቋማት በተለይም Colorado Department of Public Health and Environment (CDPHE) እና ከ Denver Department of Public Health and Department (DDPHE) ጋር በመተባበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባሮች አከናውኖአል፡ አሁንም በማከናወን ላይ እንገኛለን፡ ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ማስታወቂያ በማውጣት ትብብራችሁን ስንጠይቅ እንደነበር ይታወሳል።

  1. ክትባት የሚሰጥባቸውን ቦታዎች በማዘጋጀት በተለያዪ ጊዜያት ቁጥራቸው ከ10 ሺህ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ክትባት እንዲወስዱ ተደርጓል

  2. በኮቭድ ቫይረስ ተጠቅተው ከስራ ውጪ ሆነው ሲያገግሙ ለነበሩ በርካታ ወገኖቻችን በማህበረሰባችን ውስጥ ፈቃደኛ ኢትዮጵያን ያዘጋጁትን ምግብ በየቤታቸው ድረስ በማድረስ ብዙ ሰዎች እንዲረዱ ተደርጓል.

  3. የተለያዮ መድረኮችን በማዘጋጀት ኮቭድ የሚያስከትለውን ችግርና መደረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎ በተመለከተ በተለያዪ ጊዜያት ባለሙያዎችን በመጋበዝ ትምህርት እንዲሰጥ አድርጓል

  4. ስለ ኮቭድ መረጃ የያዙ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀትና በማሰራጨት ህብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅና እንዲከላከል ትምህርት ተሰጥቷል

  5. እስካሁንም ድረስ ኮቭድ Self-test kit እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን በተለያዩ ቦታዎች በማሰራጨት ህብረተሰቡ እንዲጠቀም እየተደረገ ነው

ከላይ የተዘረዘሩት አብዛኛዎቹ ስራዎች የተሰሩት በበጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ የቁሳ ቁስ ድጋፍና በተጨማሪም ደግሞ ከመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በተደረገልን መጠነኛ የገንዘብ ድጋፍ (grant) በመታገዝ ነው. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛውን ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ የምንገኘው Self-test kit እና ማስክ ማስራጨት ሲሆን በዚህ ስራ ለማገዝ ፈቃደኛ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን የኮሚኒቲውን ጽ/ ቤት ከዚህ በታች በተገለጸው የስልክ ቁጥር ወይም በኢሜል አድራሻ ግንኙነት በመፍጠር መተባበር የምትችሉ መሆናችሁን እየገለጽን; በፈቃደኝነት ላይ በመመስረት ለምታደርጉት ትብብር በተቻለ መጠን በስራ ላይ ለምታጠፉት ጊዜ ክፍያ (reimbursement) እንድታገኙ የምናደርግ መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን.

በዚህ አጋጣሚ እስከ ዛሬ ድረስ ስናደርግ ለነበረው እንቅስቃሴ ከጎናችን በመሆን ለረዳችሁንና ወደፊትም ለምትረዱን ከፍ ያለ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን

How can I protect myself from COVID-19 Virus

Nothing said I love you than a Good Health

የቢሮ ስልክ: 303-955-1031

ቢሮ አድራሻ 1450 S Havana Street Suite#242  Aurora, CO 80012

ኢሜል፡ Contact@ethioco.org .etcomcolorado@gmail.com

Let’s Work Together

  • Facebook
  • Twitter
Thanks for submitting!
bottom of page