እራሴን እንዴት መጠብቅ እችላለሁ?
እጆቼን ማጽዳት ለምን ያስፈልገኛል? (Why do I need to clean my hands?)
እጃችሁን ማጽዳት (የእጅ ንጽሕና ተብሎም ይጠራል) ተህዋሲያን እንዳይዛመቱ ለማቆም በጣም ጥሩ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው። ተህዋሲያን የሚዛመቱበት ዋናው መንገድ በእጃችን ነው። ስልኮችን፣ የበር እጀታዎችን እና የደረጃ እጀታዎችን ጨምሮ በሁሉም ቦታ ማለት ይቻላል ተህዋሲያኖችን ሊያነሱ ይችላሉ። እነዚህን ተህዋሲያን ምንም ሳያውቁት በሆስፒታል፣ በክሊኒክ ወይም በሌላ የጤና ተቋም ሊያሰራጩ ይችላሉ። እጆችዎ ንጹህ ሊመስሉ ይችላሉ፣ ግን አሁንም ኢንፌክሽኖችን የሚያመጡ ተህዋሲያን ሊኖሩ ይችላሉ። እጆችዎን ለማጽዳት ሲረሱ ወይም በደንብ ካላጸዷቸው፣ ተህዋሲያኖች ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያሰራጩ ይችላሉ። እንዲሁም እጆችዎ ንጹህ ካልሆኑ እና ዓይኖችዎን፣ አፍዎን፣ አፍንጫዎን ወይም በሰውነትዎ ላይ የተቀቆረጠ ቆዳን የሚነኩ ከሆነ ተህዋሲያኖችን ወደ ራሰዎ ሊያስተላልፉ ይችላሉ። የቤተሰብዎ አባላት፣ ጎብኚዎች እና የጤና እንክብካቤ ቡድን እርስዎን በሚጎበኙበት ጊዜ ሁሉ ወይም በእንክብካቤዎ ሲረዱዎት እጃቸውን እንዲያጸዱ ማበረታታት አስፈላጊ ነው። በጤና እንክብካቤ ተቋማት ውስጥ ኢንፌክሽኖችን የሚያስከትሉ ተህዋሲያኖችን ስርጭትን ለማስቆም ያግዙ።
የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰድኩ ጭምብል ማድረግ ያስፈልገኛልን? (Do I need to wear a mask if I’ve had the COVID-19 vaccine?)
የኮቪድ-19 ክትባት ቢወስዱም ጭምብል መቼ መልበስ አንዳለቦዎት ሚያሳይ መመሪያዎችን መከተልዎን ይቀጥሉ፡፡ ክሊኒካዊ ሙከራዎች እንደሚያሳዩት የኮቪድ-19 ክትባቶች ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ በጣም ጠቃሚ መንገድ ናቸው፡፡ ግን የእነሱ ጥበቃ 100% ሳይሆን ከ 94% እስከ 95% ነው፡፡ ይህ ማለት ከ 100 ውስጥ 5 ወይም 6 ሰዎች የሚመከረውን የክትባት መጠን ቢወስዱም አሁንም ቢሆን በኮቪድ-19 ሊያዙ ይችላሉ፡፡ እኛ አሁንም መከላከያው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ወይም ክትባቱ የኮቪድ-19 ስርጭትን ምን ያህል እንደሚገታ አናውቅም፡፡ ለዚህ ነው የሚመከሩ የማህበረሰብ ጠና እርምጃዎችን፣ እንደነ ጭምብል ወይም ሌሎች እርስዎን ለመጠበቅ የሚያግዙ መሳሪያዎችን መቼ እንደሚለብሱ መመሪያዎችን መከተል፣ እጅዎን ብዙ ጊዜ መታጠብ፣ ከሌሎች 2 ሜትር ርቀው መቆየት እና በሚታመሙበት ጊዜ በቤትዎ መቆየት የመሳሰሉትን መተግበር ያለባቸው፡፡ ክትባቱን ቢወስዱም እንኳ እነዚህ እርምጃዎች የኮቪድ-19 ስርጭትን ይከላከላሉ፡፡
Comments